Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የአረንጓዴ አሻራና በክረምት የበጎ ፍቃድ መርሃ ግብር የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ መርሃ ግብርን አስጀመሩ፡፡
ሚኒስትሯ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንና ከሌሎች ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ከተመደቡ የበጎነት ለአብሮነት አባላት ፣ከአከባቢው ነዋሪዎች ጋር በመሆን ነው የአረንጓዴ አሻራና በክረምት የበጎ ፍቃድ መርሃ ግብር የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ተግባር ያስጀመሩት፡፡
ወይዘሮ ሙፈሪሃት በዚህ ወቅት እርስ በእርስ የመደጋገፍና የመረዳዳት ኢትዮጲያዊ እሴቶቻችንን አጠናክረን መቀጠል አንድነታችንን ለማጠናከር የዘላቂ ሰላማችን አንድ አካል የሆነውን የአካባቢ ሰላም ግንባታ ተግባርን ማሳኪያ መንገድ ነው ብለዋል፡፡
በቀጣይነትም በተደራጀ ሰፊ ንቅናቄ የተፈናቃይ ወገኖችን ጎጆዎች ለመቀለስ፣ ለመጠገን ሰፊ ርብርብ በማድረግ ላይ እንገኛለን ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡
የጀመርናቸው የበጎ ፍቃድ ተግባራት ያሉብንን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉ መልካም ጅምሮች ናቸው ያሉት ሚኒስትሯ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ጠቁመዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.