Fana: At a Speed of Life!

የህክምና መሳሪያዎችን በሀገር ውስጥ በመስራት18 ሽልማቶችን ያገኘው ወጣት

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጣቱ ሀብታሙ አባ ፎጊ ይባላል። የመጀመርያና የሁለተኛ ድግሪ ትምህርቱን በባዮ ሜዲካል ኢንጅነሪንግና በንግድ አመራር በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተከታትሏል።
በከፍተኛ ገንዘብ ከውጭ ሀገር የሚገቡ የህክምና መሳሪያዎችን በሀገር ውስጥ ማምረት በሚቻልበት ሂደት ላይ ምርምር የሚያደርገው ይህ ወጣት÷ የመጀመሪያውን የጨቅላ ህፃናት ማሞቂያ መሳርያ በተሳካ ሁኔታ በሀገር ውስጥ መስራት ችሏል።
በዚህም በ2015 ዓ..ም የአፍሪካ ኢንተርፕረነር ሺፕ አሸናፊ በመሆን ከአፍሪካ ባንክ ባገኘው 25 ሺህ ዶላር የስንቦና አፍሪካ ጤና ጥበቃ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በማቋቋም ከሌሎች 12 የሙያ አጋሮቹ ጋር እየሰራ ይገኛል።
ሀብታሙ ከጨቅላ ህፃናት ማሞቂያ መሳሪያ በተጨማሪ ከሙያ አጋሮቹ ጋር በመሆን የኦክስጅን ማምረቻ መሳሪያና የኮሮና ቫይረስና ሌሎች በአይን የማይታዩ ተህዋሲያንን ያለ ኬሚካል የሚያፀዳ ማሽን በሀገር ውስጥ ሰርቷል።
ወጣቱ ሀብታሙ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረገው ቆይታ÷ እነዚህ የህክምና መሳሪያዎች በከፍተኛ ጥራት በሀገር ውስጥ ተመርተው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ተናግሯል።
በቴክኖሎጂው ዘርፍ የ2020 የአፍሪካ ወጣቶች ሽልማት አሸናፊ የሆነው ሀብታሙ በአሜሪካን፣ በካናዳ፣ በሞሮኮ፣ በደቡብ አፍሪካ፣ በናይጄሪያ፣ በጋና፣ በኬንያና በሀገር ውስጥ በአጠቃላይ 18 ሽልማቶችን አግኝቷል።
ከሽልማቶቹ ውስጥም አራቱ በዚህ አመት ያገኛቸው መሆኑን ነው የገለጸው።
ሀብታሙ በአሁኑ ወቅት ከሙያ አጋሮቹ ጋር በጅማ ዩኒቨርሲቲ በህክምናው ዘርፍ የተለያዩ የምርምር ስራዎች እየሰራ ይገኛል።
በቀጣይም ኢትዮጵያ በዘርፉ የሚገጥማትን ችግር ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰራ ነው የተናገረው።
በሙክታር ጠሃ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.