Fana: At a Speed of Life!

”የዳያስፖራው ተሳትፎ፣ ለሀገራችን የሳይበር ደህንነት” በሚል ርዕስ ምክክር ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ”የዳያስፖራው ተሳትፎ፣ ለሀገራችን የሳይበር ደህንነት”በሚል ርዕስ የምክክር መድረክ ነገ ይካሄዳል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ከዳያስፖራው ማህበረሰብ ጋር በነገው ዕለት የምክክር መድረክ ያካሂዳል፡፡

በዕለቱ በሳይበር ደህንነት ዘርፍ የእውቀትና ቴክኖሎጂ ባለቤትነት በማረጋገጥ፣ ሥልጠናዎችን በመስጠት፣ በሳይበር ደህንነት ኢንቨስትመንት በመሰማራትና በሌሎች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፎች የዳያስፖራው ማህበረሰብ ሊኖረው በሚችለው አስተዋጽኦ ዙሪያ ገለጻ፣ ምክክር እንዲሁም የዲጂታል ኤግዚቢሽን እና የታለንት ማዕከል ጉብኝት እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

ከኤጀንሲው ጋር ከዚህ ቀደም በተለያዩ አግባቦች ግንኙነት የፈጠሩም ይሁን ሌሎች ከኤጀንሲው ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎቱ ያላቸው የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በውይይቱ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.