Fana: At a Speed of Life!

የጅማ ከተማ አስተዳደር 10 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት መኖሪያ ለመገንባት ለተደራጁ ማህበራት አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅማ ከተማ አስተዳደር 10 ነጥብ 3 ሄክታር መሬት መኖሪያ ለመገንባት ለተደራጁ 28 ማህበራት አስረከበ።

ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ አስፈላጊውን መስፈርት አሟልተው በተለያዩ የአሰራር ችግሮች የቤት መስሪያ መሬት ያላገኙ 629 አባላትን ያቀፉ 28 ማህበራት ናቸው የዚህ ዕድል ተጠቃሚ የሆኑት።

የጅማ ከተማ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አብዶ አባ ጊዲ ፥ የመሬት ጉዳይ ትልቁ የመልካም አስተዳደር የቅሬታ ምንጭ እንደሆነ ገልፀው ፥ ለረዥም ዓመታት በተለያዩ የአሰራር ክፍተት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የመብት ጥያቄ መመለስ እንዳልተቻለ ተናግረዋል።

በቅርቡ የተዋቀረው የፅህፈት ቤቱ ግብረ ሃይል ከዚህ ቀደም በዘፈቀደ ተቀምጠ የነበረውን ከ29 ሺህ በላይ ማህደር በዘመናዊ መልኩ ማደራጀት መጀመሩን ያብራሩት አቶ አብዶ ፥ ከ17 ሺህ በላይ ማህደር በዘመናዊ መንገድ ማሰባሰብ ተችሏል ነው ያሉት።

የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ነጂብ አባ ራያ በበኩላቸው፥ ለሁሉም ነገር አስፈላጊ የሆነው መሬት የኪራይ ሰብሳቢዎች የገቢ ማከማቻ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

በቅርቡ የከተማ አስተዳደሩ ከመሬት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ የአስራር ግድፈቶችን በማስተካከል ከ7 ዓመት በላይ ጥያቄያቸው ላልተመለሰ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የፀጥታ አካላት፣ የመንግስት ሰራተኞች በሶስት ቀበሌዎች የተዘጋጀ መሬት መሰጠቱን ተናግረዋል።

የዕድሉ ተጠቃሚዎችም መሬቱን በፍጥነት እንዲያለሙም ጥሪ አቅርበዋል።

በተመስገን አለባቸው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.