Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አፍሪካ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እና ድምፅ ሊኖራት ይገባል- ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ህዝብ ያላት አፍሪካ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እና ድምፅ ሊኖራት ይገባል አሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአፍሪካ አገራት በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የተሻለ ውክልና እንዲያገኙ የሚጠይቀውን ንቅናቄ ተቀላቅለዋል።
ንቅናቄው የአፍሪካ አገራት በፀጥታው ምክር ቤት የተሻለ ተሰሚነት እና ቋሚ መቀመጫ እንዲያገኙ የሚጠይቅ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።
በዚህ ንቅናቄ አፍሪካን በተመለከተ የሚወሰኑ ውሳኔዎች ከአፍሪካ ውክልና ውጭ መወሰን እንደሌለባቸውም አስምረውበታል።
Exit mobile version