Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሸባሪው ህወሓት የኮምቦልቻ ደረቅ ወደብን ማውደሙ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በኮምቦልቻ የሚገኘውን ደረቅ ወደብ ተርሚናል ላይ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ዘረፋና ውድመት ማድረሱን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት አስታወቀ፡፡
የኮምቦልቻ የደረቅ ወደብ ተርሚናል ከ251 በላይ የደንበኛ ንብረቶችን የያዙ ኮንቴይነሮች መዘረፋቸውንም የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የወደብ እና ተርሚናል አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ምህረተአብ ተክሉ ገልጸዋል።
አሸባሪ ቡድኑ ከዚህ ቀደም ሲያደርገው እንደነበረው ወደቡ ላይም የቻለውን በመዝረፍ ያልቻለውን ደግሞ ማውደሙን አቶ ምህረተአብ ተክሉ አስረድተዋል።
በተጨማሪም በደረቅ ወደቡ ንብረት የነበራቸውን ግለሰቦች በማግኘት እንደሚያነጋግሯቸው አቶ ምህረት መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version