Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በጋምቤላ ክልል 1 ሺህ 48 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመስኖ ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል አሸባሪውን ህወሓት እና ተላላኪዎቻቸውን ከማጥፋት ጎን ለጎን የልማት ስራዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሠራ የክልሉ ርዕሠ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ገለፁ።
በአፍሪካ ቀንድ የስደተኞች ተጽዕኖ ምላሽ የልማት ፕሮጀክት በጀት ድጋፍ በኢሌይ-ኢቸዋይ፣ በባዚየልና በአቹዋሃ የሚገነቡ የአነስተኛ መስኖ ግንባታ ፕሮጀክቶች የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል።
የማህበረሰቡ የኑሮ መሰረት ግብርና በመሆኑ በመስኖ እንዲጠቀሙ በማድረግ በአመት ሁለትና ከዛ በላይ እንዲያመርቱና በግለሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡ ማስቻል እንደሚገባ ርዕሠ መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡
የመስኖ ግንባታዎቹ በተያዘላቸው የስምንት ወራት ጊዜ ገደብ ውስጥ መጠናቀቅ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አጃክ ኡቻላ በበኩላቸው÷ ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ 262 ሄክታር መሬት እንደሚያለሙና 1 ሺህ 48 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
ፕሮጀክቶቹ 242 ሚሊየን 912 ሺህ 251 ብር በሆነ ወጪ እንደሚገነቡም ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version