Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

መንግስት ለሀገር ውስጥ መድሃኒት አምራች ኢንዱስትሪዎች አስፈላጊውን ትብብር ለማድረግ ቁርጠኛ ነው – ዶ/ር ሊያ ታደሰ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ እና የኢትዮጵያ መድሃኒት እና የህክምና ቁሳቁሶች አምራች ማህበራት በዛሬው ዕለት ጥራት ያለው የመድሃኒት አቅርቦት በተፈለገው ጊዜ ለዜጎች ለማድረስ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

በስምምነት ሥነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፥መንግስት ሀገር በቀል አምራች ኢንዱስትሪዎችን የማበረታት እና የማሳደግ ስራ ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሁለቱ ተቋማት ስምምነት፥ ጥራት ያለው የመድሃኒት አቅርቦትን በተፈለገው ጊዜ ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ያስችላል ነው ያሉት ሚኒስትሯ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ለሀገር ውስጥ መድሃኒት አምራች ኢንዱስትሪዎች አስፈላጊውን ትብብር ለማድረግ ቁርጠኛ እንደሆነም ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version