Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በጋምቤላ ከተማ ባጃጅ ውስጥ 9 ክላሽንኮቭ የጦር መሣሪያ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ከተማ ቀበሌ 03 አንድ ግለሰብ በሚያሽከረክረው ባጃጅ ውስጥ 9 ክላሽንኮቭ የጦር መሣሪያ ተያዘ፡፡
ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት እንግዳው ተሻገር የተባለ ግለሰብ በሚያሽከረክረው ባጃጅ ውስጥ እንደሆነ መረጃውን ከስፍራው ያደረሱን ታማኝ የመረጃ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡
ግለሰቡን በጥብቅ ዲሲፕሊን ክትትል በማድረግ የደህንነት ሰዎች ሚና ከፍተኛ እንደነበር የገለፁት የመረጃ ምንጮቻችን፥ የፌዴራል ፖሊስ እና የጋምቤላ ክልል ፖሊስ በጥምረት ግለሰቡን ጨምሮ የተለያዩ ህገ-ወጦችን በቁጥጥር ስር እያዋሉ እንደሆነ ተናግረዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version