Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በማሊ በተፈጠረ ግጭት ወታደሮችን ጨምሮ 30 ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 7፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በማሊ በተፈጠሩ የተለያዩ ግጭቶች 30 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰማ።

ግጭቱ በማሊ የኦጎሳጎ መንደርን ጨምሮ በሶስት የተለያዩ ስፍራዎች የተቀሰቀሰ ነው።

ከሞቱት 30 ሰዎች ውስጥ ዘጠኝ ወታደሮች በወታደራዊ ጣቢያ ላይ በተፈጸመ ጥቃት ተገድለዋል።

21ዱ ሰዎች ደግሞ ታጣቂዎች መንደር ውስጥ በፈጸሙት ጥቃት መገደላቸው ታውቋል።

ግጭቱ የተፈጸመበት መንደር በአብዛኛው ከፉላኒ ጎሳ የሆኑ ሙስሊሞች የሚበዙበት አካባቢ መሆኑ ይነገራል።

ግጭቱን ሰበብ አድርጎ ለተፈጸመው ጥቃት ሃላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም የአካባቢው ባለስልጣናት ግን በስፍራው የሚንቀሳቀሱ ፅንፈኛ አሸባሪ ቡድኖች ከግጭቱ ጀርባ ሳይኖሩበት እንደማይቀር ገልጿል።

በአካባቢው በሚከሰት ተደጋጋሚ የጎሳ ግጭት ምክንያት በርካቶች ለህልፈት እንደሚዳረጉ መረጃዎች ያመላክታሉ።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version