Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዩኒሴፍ ከ7 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የትምህርት ግብዓቶችን ለጋምቤላ ክልል ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) በጋምቤላ ክልል የትምህርት ተደራሽነትና ጥራትን ለማሻሻል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ከ7 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸውን የተለየዩ የትምህርት ግብዓቶችን ድጋፍ አደረገ።
 
ድጋፉን ለክልሉ ያስረከቡት በዩኒሴፍ የጋምቤላ ተጠሪ ዶክተር አብዱልሃቅ ዋዊድ እንዳሉት÷ድርጅቱ በክልሉ የትምህርት ተደራሽነትና ጥራትን ለማሻሻል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የትምህርት ተቋማት ግንባታን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ነው።
 
ለእዚህም በተያዘው የትምህርት ዘመን በክልሉ የአምስት ትምህርት ቤቶችን ግንባታ ጨምሮ የተለያዩ የትምህርትና የተማሪዎች ንጽህና መጠበቂያ ግብዓቶችን ድጋፍ ማድረጉን ጠቅሰዋል።
 
ትናንት ደግሞ ከ7 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸውና የትምህርት ተቋማት በሌለባቸው አካባቢዎች የሚያገለግሉ ተንቀሳቃሽ የትምህርት መስጪያ ድንኳኖች፣ በርቀት ትምህርትን ለመከታተል የሚስያስችሉ ራዲዮኖች እና የተማሪ ቦርሳዎችን መለገሳቸውን አስታውቀዋል።
 
በተጨማሪም የተማሪ ንፅህና መጠበቂያ ፣ የቅድመ መደበኛ የትምህርት “ኪቶች” እና ሌሎች የትምህርት ግብዓቶችም በድጋፉ እንደሚገኙበት ዶክተር አብዱልሃቅ አመልክተዋል።
 
“በቀጣይም ለክልሉ ሕጻናት ጥራቱን የጠበቀ የትምህርት አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ድርጅቱ የጀመረውን ደጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version