Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለሀገራችን የምናደርገውን ድጋፍ አጠናክረን እናስቀጥላለን- በግሪክ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በግሪክ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለወገን የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገለፁ፡፡
ወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ በአቴንስ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት ተካሂዷል።
የኢትዮጵያ መንግስት አሸባሪው ህወሓት በከፈተው ጦርነት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የሚያደርጉትን የገንዘብ ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ እና በምዕራባውያን ሀገራትና ድርጅቶች በአገራችን ላይ የከፈቱትን ጫና ለመመከት በሚደረገው አለም አቀፍ እንቅስቃሴ ንቁ ተሳታፊ ሊሆኑ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም ለዳያስፖራው በተደረገው ጥሪ መሰረት አገራዊ ኮሚቴ ተዋቅሮ ሰፊ ዝግጅት እየተደረገ ስለሆነ÷ ጥሪውን ተቀብለው አገራቸውን እንዲጎበኙና ሲሄዱም ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ የሚሆን ነገር ይዘው እንዲሄዱ ጥሪ ቀርቧል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው÷ በጦርነቱ የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት እንዲሁም የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደቀያቸው ለመመለስ መንግስት የሚያደርገውን ጥረት በገንዘብ እንደሚደግፉ እና ወደ ሀገር ቤት የሚልኩትን ገንዘብ በህጋዊ መንገድ በመላክ ከሀገራቸው ጎን እንደሚቆሙ ማረጋገጣቸውን በጣሊያን ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version