Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች የዘማቾች ቤተሰቦችን ሰብል ሰበሰቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እንዲሁም የተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች በወልመራ ወረዳ የዘማቾች እና አቅመደካማ አርሶአደሮን ሰብል ሰበሰቡ፡፡
በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የቋንቋና ባህል ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወርቅነሽ ብሩ÷ የሀገርን ደህንነት ለማስጠበቅ፣ ለጸጥታ ሥራ እና ለዘመቻ የተሰማሩ አርሶ አደሮችን ሰብል መሰብሰብ አንዱ የዘመቻው አካል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የወልመራ ወረዳ አስተዳደሪ በቀለ ተስፋዬ በበኩላቸው÷ ዘማችና ሚሊሻዎች የሰላምና የጸጥታ ሥራ እየሠሩ ባለበት ሁኔታ የእነርሱን ሰብል መሰብሰብ በመቻሉ መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡
የወልመራ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ ደሳለኝ ተሾመ እንደገለፁት÷ በፈለጮ ቀበሌ ቦራአ ጎጥ ሶስት ሄክታር የስንዴ ሰብል፣ የ6 ዘማች አርሶአደሮች እና የሚሊሻ ቤተሰቦች እንዲሁም የአቅመ ደካማ አርሶ አደሮች ሰብል ተሰብስቧል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version