Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

“ኔቶ” ዲፕሎማሲያዊ አማራጮችን እንዲያጤን ሩሲያ መከረች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኔቶ ወደ ምሥራቅ የሚያደርገውን መሥፋፋት ገትቶ ዲፕሎማሲያዊ አማራጮች ላይ ቢያተኩር እንደሚበጅ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን መከሩ፡፡

ሩሲያ ኃይፐርሶኒክ ሚሳኤል እያበለጸገች እንደምትገኝ እና ከምዕራባውያኑም ሆነ ከዩክሬን ለሚቃጣ ማንኛውም ዓይነት የደህንነት ሥጋት አጸፋዊ ምላሽ እንደምትሰጥ አስጠንቅቃለች፡፡

ሩሲያ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን ድንበር ከማስጠጋቷ ጋር ተያይዞም አሜሪካ እና ብሪታንያ በዩክሬን ላይ ጥቃት ሊሰነዘር ይችላል የሚል ስጋት እንደገባቸው ሲገልጹ ኔቶ ደግሞ በጉዳዩ ላይ ሩሲያ አዝማሚያዋን እንድታስረዳ ጠይቋል፡፡

በሌላ በኩል የሩሲያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰርጌይ ላቭሮቭ፥ ኔቶ ወደ ሩሲያ ድንበር አቅራቢያ ወታደራዊ መሣሪያዎችን እያስጠጋ ነው ሲሉ ኅብረቱን ከሰዋል፡፡

ቭላድሜር ፑቲን በበኩላቸው÷ በኔቶ በኩል ሀገራቸው ላይ ከሚፈጸመው ጫና በተጨማሪ ምዕራባውያኑ ቻይናን የደህንነት ሥጋት ናት የሚሉትንም ጽንሠ-ሃሳብ እንደማይቀበሉና ፍረጃው ከዓለም አቀፉ ህግ እንደሚጻረር ነው ያሰመሩበት፡፡

ቻይናን ለማስፈራራት አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና አውስትራሊያ የፈጠሩትን ጥምረትም ኮንነው በምክክር ነገሮችን ከማርገብ ይልቅ እንዲህ ዓይነት አዝማሚያዎች የበለጠ ቀጣናዊ ውጥረቱን ያባብሱታል ሲሉ ፑቲን መምከራቸውን ሲጂቲ ኤን አስነብቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version