Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ማራቶን ሞተርስ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ማራቶን ሞተርስ 20 በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሸከርካሪዎችን እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ በዛሬው እለት አስመርቋል፡፡
የተመረቁት 20 ተሽከርካሪዎች በኤሌክትሪክ የሚሰሩ እና “ሃንዳ ኮይና “እና “ሃንዳ አዮንክ” የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ናቸው፡፡
ተሽከርካሪዎቹ እያንዳንዳቸው እስከ 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር እንደሚያወጡም ተገልጿል፡፡
በኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚሰጡ እና ከነዳጅ ነፃ በመሆናቸው ሀገሪቱ ለነዳጅ የምታወጣውን የውጭ ምንዛሬ ከመቀነስ ባለፈ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ መደገፍ የሚያስችሉ ናቸው ተብሏል፡፡
ማራቶን ሞተርስ በ2023 ዓ.ም 50 በመቶ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን እንዲሁም በ2025 ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን እውን የማድረግ እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በቅድስት ብርሀኑ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version