Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የወርቅ ማዕድን ምርት በተገቢው ልክ ለገበያ እየቀረበ አይደለም ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን የወርቅ ማዕድን ምርት ለሃገር አስተዋፅኦ በሚያበረክት መልኩ ለገበያ እየቀረበ አለመሆኑ ተገለፀ፡፡
የክልሉ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር በየነ በላቸው፥ በክልሉ ባለው የማዕድን ሀብት ልክ አካባቢውም ሆነ ሀገር ተጠቃሚ ሳይሆኑ መቆየታቸውን ተናግረዋል።
በማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር የባህላዊ ማዕድናት ምርት ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጂክሳ ኪዳኔ በክልሉ ወርቅ በሚመረትበት ቤሮ ወረዳ የሚስተዋሉ ችግሮችን አንስተዋል።
ህገወጥ ንግድ፣ ያልዘመነ ማምረቻ መሳሪያ መጠቀም፣ አቅራቢዎች በገቡት ውል ልክ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አለማቅረብ ከሚያጋጥሙ ችግሮች መካከል ናቸው ብለዋል።
በቀጣይ በቤሮ ወረዳም ሆነ በሌሎች ማዕድናት በሚገኙባቸው የክልሉ አከባቢዎች የሚስተዋሉ ችግሮችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በአፋጣኝ መፍትሄ እንደሚሰጠውም የቢሮ ሃላፊው ገልፀዋል።
በደቡብ ምዕራብ ክልል ከፍተኛ የሆነ የወርቅ፣ የብረትና የድንጋይ ከሰል ማዕድናት መኖሩም ተገልጿል፡፡
በአለማየሁ መቃሳ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version