Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ገረገራ፣ ፍላቂት እና አቃት ከተሞች ተቋርጦባቸው የቆየውን የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም አገኙ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ወሎ ዞን በሚገኙት ገረገራ ፣ ፍላቂት እና አቃት ከተሞች ለአምስት ወራት ያህል ተቋርጦባቸው የቆየውን የኤሌክትሪክ ኃይል መልሰው እንዲያገኙ ተደርጓል።
ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰሜን ወሎ ዞን ከተሞች ያደረሰው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ጉዳት እና ውድመት ከፍተኛ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።
በተቋሙ አመራር እና በሰራተኞች ያላሰለሰ ጥረት ከታህሳስ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ቀናት ጋሸና፣ ኮን እና ዳውንት ከተሞች ኃይል ማግኘታቸው ይታወቃል።
በዛሬው እለትም በሶስቱ ከተሞች የደረሰውን ውድመት በመጠገን የኤሌክትሪክ አገልግሎቱን ማስጀመሩን ገልጿል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version