Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ወጣቶች ህብረት በስዊዘርላንድ ያሰባሰቡትን 35 ሺህ የስዊዝ ፍራንክ አስረከቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በስዊዘርላንድ የኢትዮጵያ ወጣቶች ህብረት ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለመርዳት “የገና ስጦታ ለእናት አገሬ” በሚል በቶምቦላ ሎተሪ እጣ ያሰባሰቡትን 35 ሺህ የስዊዝ ፍራንክ ለቋሚ ጽ/ቤቱ አስረክበዋል፡፡
በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዘነበ ከበደ÷ በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጊዜያቸውን፣ ገንዘባቸውንና ጉልበታቸውን ሳይቆጥቡ ለአገራቸው ድጋፍ ሲያደረጉ ይህ የመጀመሪያቸው እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡
በተለይ አሸባሪው ህወሃት ቡድን ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር በማበር በአገር ሉዑላዊነትና በህዝቦች ደህንነት ላይ ጥቃት ከከፈተበት ጊዜ ጀምሮ በአገር ፍቅርና በፍጹም ኢትዮጵያዊ አንድነት ስሜት የታየው ቁጭት፣ መነሳሳትና ተሳትፎ እጅግ ሚያኮራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በቀጣይም በተናጥልም ይሁን በጋራ የሚደረገው ድጋፍ ሳይበታተን በተቀናጀ ሁኔታ ወደ አንድ ቋት እንዲገባ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version