Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዳግም ወደ ላልይበላ በረራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላልይበላ የሚያደርገውን የሀገር ውስጥ በረራ በድጋሚ በዛሬው ዕለት ጀምሯል፡፡
አሸባሪው እና ወራሪው ህወሓት በላልይበላ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ከፍተኛ ዝርፊያና ውድመት መፈጸሙን ተከትሎ አየር መንገዱ ወደ ከተማዋ የሚያደርገውን በረራ አቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
 
በዛሬው ዕለትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በድጋሚ ወደ ላልይበላ የሚያደርገው በረራ በይፋ መጀመሩን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከአየር መንገዱ ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በመላኩ ገድፍ
 
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version