Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በጦርነቱ ምክንያት ውድመት ደርሶበት የነበረው የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በከፊል አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦርነቱ ምክንያት ውድመት ደርሶበት የነበረው የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በከፊል አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገለጸ፡፡

የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ አራጋዉ ግዛው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ፥ ሆስፒታሉ ከፍተኛ ውድመት የደረሰበት ቢሆንም ከመንግስትና ከግል ተቋማት ድጋፎች እየተደረገለት መሆኑን አንስተዋል፡፡

ሆስፒታሉ ከሰሞኑ ከወራቤ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባገኘው ድጋፍ የተመላላሽና ድንገተኛ አገልግሎቶችን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶችን መጀመሩን ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡

በሆስፒታሉ የቀዶ ህክምና አገልግሎት ለመጀመር የህክምና መሳሪያ ችግር መኖሩን የገለጹት አቶ አራጋው ፥ በመንግስት የሚደረገው መልሶ ግንባታ እንዲቀጥል ጠይቀዋል ፡፡

በሰላማዊት ሙሉነህ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version