Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለመጀመሪያ ጨዋታ ልምምዱን አጠናክሮ ቀጥሏል

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 29፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እሁድ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ከኬፕ ቨርዴ ጋር ለሚያደርገው የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመርያ ጨዋታ ልምምዱን በተጠናከረ ሁኔታ ማከናወኑን ቀጥሏል።

በዛሬው የልምምድ መርሐ ግብር ላይም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሐፊ አቶ ባሕሩ ጥላሁን ተገኝተው ቡድኑን መመልከታቸውን ከፌደሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኑ ቀደም ሲል በካሜሮን ዋና ከተማ አኔክስ 2 በተባለው የልምምድ ሜዳ  ልምምድ ሲያደርጉ መቆየቱ የሚታወስ ነው ።

Exit mobile version