Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጥምቀትን በጎንደር ከዳያስፖራው ጋር ለማክበር አስፈላጊው ቅደመ ዝግጅት ተጠናቋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥምቀትን በጎንደር ከዳያስፖራው ማኅበረሰብ ጋር በድምቀት ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ሥራ ማጠናቀቁን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
 
በቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ፕሮሞሽንና ግብይት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በሰጡት መግለጫ÷በጎንደር በሚከበረው የጥምቀት በዓል የኪነ ጥበብ ሥራዎች፣ የቢዝነስ አቅምን የሚያሳዩ ባዛሮች፣ ኤግዚብሽን፣ ፓናል ውይይት እና የከተራ ዝግጅት ይካሔዳሉ።
 
የዳያስፖራው ማኅበረሰብም በዝግጅቱ እንዲሳተፍ ሚኒስትር ዴታዋ ጥሪ ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል።
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
Exit mobile version