Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዋልያዎቹ ከቡርኪናፋሶ ጋር እያደረጉት ባለው ጨዋታ 1 ለ 0 እየተመሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከቡርኪናፋሶ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ እየተካሄደ ነው፡፡

በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ የተጠናቀቀ ሲሆን፥ ዋልያዎቹ 1 ለ 0 እየተመሩ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ሁለት የምድቡ ጨዋታዎችን መሸነፉ የሚታወስ ሲሆን፥ በአፍሪካ ዋንጫው ያለፉትን 11 ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለመጨረሻ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ ማሸነፍ የቻለው እ.ኤ.አ 1976 ኡጋንዳን ነበር ፡፡

ኢትዮጵያ እና ቡርኪናፋሶ በአፍሪካ ዋንጫ ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት እ.ኤ.አ 2013 ሲሆን፥ በወቅቱ ቡርኪና ፋሶ አራት ለአንድ በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላ ነበር ፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፤ እንገንባ፤ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version