Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአትላስ አካባቢ የተነሳው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቦሌ ክፍለ ከተማ አትላስ አካባቢ የተነሳው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን የእሳት አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋት ምላሽ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽን ኮማንደር መስፍን አያሌው ተናገሩ።
በእሳት አደጋው ከኡራኤል ቤተክርስያን ጀርባ በሚገኙ የንግድ መጋዘኖች ልዩ ልዩ የግንባታ እቃዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ፋና ቴሌቪዥን በስፍራው ተመልክቷል።
የእሳት ቃጠሎው ስምንት ሰአት ከሩብ መነሳቱን የእሳት አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋት ምላሽ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽን ኮማንደር መስፍን አያሌው ተናግርዋል፡፡
የአዲስ አበባ እሳት አደጋ መከላከል በስፍራው ተገኝቶ እየነደዱ የነበሩ እቃዎችን ውሃ እና ኬሚካል በመጠቀም ከቃጠሎ ታድጓል።
ሰው ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱን እና የአካባቢው ነዋሪ እና የጸጥታ ሃይሎች ባደረጉት ጥረት እሳቱ መጥፋቱን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል ፡፡
የደረሰው የንብረት የጉዳት መጠን በቀጣይ የሚጣራ ይሆናል ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version