Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአብዬ ሰላም አስከባሪ ኃይል ዓለም አቀፍ ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “የአብዬን ሰላም የማጠናከር ተልዕኳችንን በአስተማማኝ ወታደራዊ ዝግጁነት በውጤት እያስቀጠልን ነው” ሲሉ በአብዬ የ9ኛ ሁለገብ ሎጀስቲክስ ዋና አዛዥና የናሽናል ቲም አስተባባሪ ሌ/ኮሎኔል ክፍሎም ገ/ማርያም አስታወቁ
ዋና አዛዡ እንዳሉት፥ የሁለገብ ሎጀስቲክስ ሻምበሉ ሁለንተናዊ ዝግጁነት ከዓለም- አቀፍ የሰላም ማስከበር መመዘኛ አንፃር ጥራትና ብቃቱ በመስኩ ሙያተኞች ተገምግሞ አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።
በግዳጅ ቀጣናችን የሚገኘው ማህበረሰብ ሰላሙ ተጠብቆለት መኖር እንዲችል አድርገናል ያሉት ከፍተኛ መኮንኑ ፣ የተሰጠንን ተልዕኮ በድል እየተወጣን በመገኘታችን ኩራት ይሰማናል ብለዋል።
የሁለገብ ሎጀስቲክስ ሻምበል በአብዬ አለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ በአስተማማኝ ዝግጁነት አመርቂ ተግባር ሲወጣ የቆየ መሆኑን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመልክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version