Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በባኮ ቲቤ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ሸዋ ዞን ባኮ ቲቤ ወረዳ ሾቦካ ከተማ አቅራቢያ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
 
አደጋው ሁለት ከባድ ተሽከርካሪዎች እርስ በርስ በፈጠሩት ግጭት የተከሰተ መሆኑን ከዞኑ ከሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በተከሰተው አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ÷ግጭቱን ተከትሎ በተፈጠረው የእሳት ቃጠሎም ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተመላክቷል፡፡
 
የአካባቢው ማህበረሰብ ባደረገው ርብርብ የተነሳው እሳት በቁጥጥር ስር መዋሉ እና የትራንስፖር አገልግሎት መቀጠሉም ተገልጿል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version