Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ የተፈፀመውን ግድያ ተከትሎ እያጣራ መሆኑን የኦሮሚያ ፖሊስ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህዳር 22 ቀን 2014 በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ የተፈፀመውን ግድያ ተከትሎ የኦሮሚያ ፖሊስ እያጣራ መሆኑን አስታውቋል።
በኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ገላን ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ እስካሁን ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው በምርምራ ሂደት ላይ ይገኛል ብለዋል።
ምክትል ኮሚሽነሩ እንዳስታወቁት፥ ህዳር 22 ቀን 2014 ዓ.ም ቦሰት ወረዳ 14 ንፁሃን ዜጎች ተገድለዋል፤ ከአንድ ቀን በፊት ህዳር 21 ቀን 2014 ዓ.ም ደግሞ በፈንታሌ ወረዳ ለዘመቻ በተሰማሩ 11 የኦሮሚያ ፓሊሶች ላይ ግድያ ተፈፅሟል።
እስካሁን ግድያውን ማን እና እንዴት እንደፈፀመው በመጣራት ላይ መሆኑንም ገልጸዋል።
በምርመራ ሂደቱ መነሻ የሆኑ እና የተለዩ ጉዳዮች የተገኙ ሲሆን፥ እስካሁን ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።
በምንይችል እዘዘው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version