Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአፍሪካ ዋንጫ ካሜሮን ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀች

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ካሜሮን ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቀቀች።

ምሽቱን ለደረጃ የሚደረግ ፍልሚያ በአዘጋጇ ሀገር ካሜሮንና በቡርኪናፋሶ መካከል ተደርጓል።

ጨዋታው 3 አቻ በመጠናቀቁ ወደ መለያ ምት ያመራ ሲሆን፥ በመለያ ምት ካሜሮን ቡርኪናፋሶን 5 ለ 3 በመርታት ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

በዛረው እለትም በሴኔጋልና በግብፅ መካከል የሚደረገው የፍፃሜ ጨዋታ ይጠበቃል።

Exit mobile version