Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ከኔዘርላንድስ የውጭ ንግድ እና ልማት ትብብር ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ)የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ከኔዘርላንድስ የውጭ ንግድ እና ልማት ትብብር ሚኒስትር ሲግሪድ ካግ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም  ኔዘርላንድስ በኢትዮጵያ ለተጀመሩ ፕሮጀክቶች እና ፕሮግራሞች የምታደርገውን ድጋፍ በተመለከተ መክረዋል፡፡

ዶክተር ኤርጎጌ  የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዋና ዋና ተግባራት እና የማኅበራዊ ደህንነት ዕርዳታ ፕሮጀክቶች ማህበራዊ ጥበቃን ፣ የአካል ጉዳትን ፣ የሴፍቲኔት ፕሮግራም  ውጤታማነትን  እና  በተሻሻለው የሰራተኛ አዋጅ ዙሪያም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በተጨማሪም  የሠራተኛ አስተዳደር ዲጂታል፣ የአቅም ግንባታ፣ የተጎዱትን መደገፍ ፣ ስደት ፣ የመልሶ ማቋቋም ኔዘርላንደስ በኢትዮጵያ  እያበረከተችው ላለው  መጠነ ሰፊ  ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ፡፡

ሲግሪድ ካግ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግስት በሰራተኛና ማህበራዊ ጥበቃ ተግባራት ላይ የሚያሳየውን ቁርጠኝነት ማድነቃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

Exit mobile version