Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሕንድ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና ልምድ በማካፈል የኢትዮጵያ ታማኝ አጋር ናት – አምባሳደር ትዝታ ሙሉጌታ

Employees of Indochine Apparel PLC working in the Hawassa Industrial Park, where more than 20 global manufacturers produce textiles and appeal, in Hawassa, Ethiopia on December 15, 2018. Photo © Dominic Chavez/International Finance Corporationr

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕንድ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና ልምድ በማካፈል የኢትዮጵያ ታማኝ አጋር ናት ሲሉ በሕንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ትዝታ ሙሉጌታ ገለጹ።

በሕንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሀገሪቱ የንግድ እና የኢንዱስትሪ ምክር ቤቶች ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር “ኢትዮጵያ የ2030 የአፍሪካ የብልጽግና ችቦ” በሚል መሪ ቃል የበይነ-መረብ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በበይነ መረብ የተካሄደው ውይይት ዓላማ ፥በኢትዮጵያ እና በሕንድ መካከል ያለውን የኢንቨስትመንት እና የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በሕንድ የኢትጵያ ኤምባሲ አምባሳደር ትዝታ ሙሉጌታ ÷ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአምራች ኢንዱስትሪ መዳረሻ ለመሆን ካላት ፍላጎት አንጻር መዋዕለ-ነዋያቸውን ለሚያፈሱ ባለሐብቶች ሂደቶችን በማሳለጥ እና ማበረታቻዎችን በማቅረብ ምቹ ምህዳር መፍጠር ትቀጥላለች ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዘርፉ ላይ የኢኮኖሚ እና የህግ ማሻሻያዎችን እንዳደረገችም ጠቁመው፥ የሕንድ ባለሐብቶች በኢትዮጵያ ያልተነካ የተፈጥሮ ሐብት እና የሰው ኃይል አቅርቦት መኖሩን አውቀው መዋዕለ-ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አምባሳደር ትዝታ ÷ የሕንድ ኩባንያዎች በአፍሪካ ነጻ የንግድ እና የግብይት ሥርዓት ውስጥ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታዎችም ማመላከታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዌቢናር ውይይቱ ከፍተኛ ሥራ አስፈጻሚዎች እና በሕንድ በተለያዩ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

አምባሳደር ትዝታ የበይነ መረብ ውይይቱ ዕውን እንዲሆን ላስተባበሩ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version