Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቋሚ ሲኖዶስ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ማክሰኞ ይወያያል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በዛሬው እለት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር ለመወያየት ቀጠሮ ይዞ የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ማክሰኞ መዛወሩን ከተማ አስተዳደሩ አስተውቋል፡፡
የዛሬውን ውይይት ማስኬድ ያልተቻለውም በትናንትናው እለት የተጀመረው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጉባኤ ዛሬም በመቀጠሉ በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ከንቲባ አዳነች አቤቤ መገኘት ባለመቻላቸው ነው ተብሏል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በምክትል ከንቲባው የሚመራ የአመራር ቡድን በመንበረ ፓትሪያርኩ ፅህፈት ቤት ተገኝቶ ከብፁዓን የቋሚ ሲኖዶሱ አባላት ጋር የመከረ ሲሆን÷ በዚህም በቀጣይ ማክሰኞ ውይይት ስለሚደርግበት ሁኔታ መነጋገራቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version