Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሰላም ሚኒስቴር በአማራ ክልል በአሸባሪው ህወሓት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር በአማራ ክልል በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች 35 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
የሰላም ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዷለም የክልሉ መንግሥት ለዓመታት የገነባው መሠረተ ልማት በአሸባሪው ቡድን መውደሙን አንስተዋል።
በጦርነቱ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋም እና የወደሙ መሠረተ ልማቶችን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የፌደራል መንግሥት ከክልሉ መንግሥት ጋር ደረጃ በደረጃ እንደሚፈታ መግለጻቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
አቶ ብናልፍ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት÷ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በአፋር ለሚደረገው መልሶ ግንባታ 15 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን ጠቁመው÷ ዛሬ ደግሞ ለአማራ ክልል 35 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት÷ ኢትዮጵያውያን መተባበር ከቻልን በአሸባሪው የህወሓት ቡድን የደረሰውን ውድመት በአጭር ጊዜ መገንባት እንችላለን ብለዋል።
የሰላም ሚኒስቴር ያደረገው ድጋፍ ለመልሶ ግንባታ ሥራ ሚናው የጎላ መሆኑን ጠቁመው÷ የተደረገውን ድጋፍም መንግሥት በተገቢው መንገድ ሥራ ላይ እንደሚያውል ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን አሁንም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version