Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

እስራኤል ለኢትዮጵያ 30 ሺህ ዶላር የሚያወጡ የኮቪድ-19 መከላከያ ግብዓቶች ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል መንግስት ለኢትዮጵያ 30 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚያወጡ የተለያዩ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ግብዓቶችን ድጋፍ አድርጓል፡፡
 
ድጋፉን የተረከቡት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ÷የእስራኤል መንግስት ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
እስራኤል በጤናው ዘርፍ ለምታደርገው ድጋፍ አድናቆታቸውን የገለጹት ሚኒስትሯ÷የተደረገው ድጋፍ የኮሮና ቫይረስን የመከላከል አቅም እንደሚያሳድግ ጠቁመዋል፡፡
 
በቀጣይ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ከእስራኤል ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥልም ተናግረዋል፡፡
Exit mobile version