Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለተፈጥሮ ሀብት ህልውና አደገኛ የሆኑ አረሞችን ለማጥፋት የሁሉም አካላት ርብርብ ያስፈልጋል – የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሃብት ህልውና ላይ አደጋ የደቀኑ መጤ አረሞችን ለማጥፋት ሁሉን አቀፍ ንቅናቄ ማድረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ።
በዝዋይ ሃይቅ ላይ የተስፋፋውን የእምቦጭ አረም ለማጥፋትና በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ላይ የደቀነውን አደጋ ለመከላከል የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በባቱ ከተማ ተካሂዷል።
በዚሁ ወቅት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታሁን ጋረደው እንደተናገሩት፥ በአገሪቱ የውሃ ሀብት ላይ እየተስፋፋ ያለውን የእምቦጭ አረም ለማጥፋት የሁሉም ህብረተሰብ ትብብር ይጠይቃል።
መጤና ወራሪ አረሞችን በአንድ ተቋም ብቻ ማስወገድ እንደማይቻል ጠቁመው፥ ህብረተሰቡ፣ የተለያዩ ተቋማት፣ አደረጃጀቶች በጋራ መስራት ይገባቸዋ ብለዋል፡፡
አካባቢን ከብክለት ለመጠበቅና መጤ ወራሪ አረሞችን ለመከለካል የአስር ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ መዘጋጀቱንና ይህንንም ለመከወን የህዝብ ንቅናቄ አንዱ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ከዝዋይ ሀይቅ ላይ እምቦጭ በመንቀል የተሳተፉት የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ፕሬዚዳንት አስፋው ተክሌ እና የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ የጽህፈት ቤት ሃላፊ አክሊሉ ታደሰ እንደገለጹት÷ ወጣቱ በአካባቢ ጥበቃ ላይ ባለቤት ሆኖ መስራት እንዳለበት አስገንዝበው÷ በአገሪቱ የልማት ስራዎች ላይ በስፋት ተሳታፊ እንዲሆንም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version