Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

“ሕብረተሰባዊ የጤና ቁርጠኝነት ለጾታ እኩልነት በኢትዮጵያ” የተሰኘውን ፕሮጀክት የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሕብረተሰባዊ የጤና ቁርጠኝነት ለጾታ እኩልነት በኢትዮጵያ” የተሰኘው ፕሮጀክት የማስጀመሪያ መርሀ ግብር በጅግጅጋ ከተማ ተካሄደ።

ፕሮጀክቱ ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ክልሎች በጤናው ዘርፍ ከፍ ለማድረግ እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡

በአራት ክልሎች ላይ የሚተገበረው ይህ ፕሮጀግት በሶማሌ ክልል በአራት ዞኖች ማለትም በሸበሌ ዞን ፣ በሲቲ ፣ በፊቅና ሞያሌ እንደሚተገበር ተነግሯል።

የክልሉ ሕብረተሰብ ከፊል አርብቶ አደር እንደመሆኑ መጠን በሚቀሳቀሱበት ቦታ ሁሉ የዚህ ፕሮጀክት ተጠቃሚ በመሆን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናል ተብሏል።

ፕሮጀክቱ ለ3 ዓመት የሚተገበር ሲሆን÷ በተያዘለት ቀነ ገደብ አልቆ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ እንሚደረግም ተመላክቷል፡፡

በመርሀ ግብሩ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ፥ ፕሮጀክቱ ስኬታማ እንዲሆን በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ማለታቸውን ከሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙኃን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ፕሮጀክቱ በቤሻንጉል ጉምዝ፣ አፋር እና ጋምቤላ ክልሎችም ተግባራዊ እንደሚደረግ በመርሃ ግብሩ ላይ ተጠቁሟል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version