Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በዩክሬን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከመንቀሳቀሳቸው በፊት ጀርመን ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር እንዲመካከሩ ኤምባሲው አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን በርሊን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዩክሬን በትምህርት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ከመንቀሳቀሳቸው በፊት ለኤምባሲው እንዲያሳውቁ አሳሰበ፡፡

ኤምባሲው በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እና ችግር እንደሚረዳና ኢትዮጵያውያን ከመንቀሣቀሣቸው በፊት ለደኅንነታቸው ሲባል በማንኛውም ጊዜ በ+491767269094 የሞባይል ስልክ ቁጥር እና በ berlin.embassy@mfa.gov.et ኢሜይል አድራሻ በመጠቀም ኤምባሲውን እንዲያገኙ እና እንዲመካከሩ አሳስቧል፡፡

ከትናንት ጀምሮ ሩሲያ በዩክሬን ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄደች መሆኑ ይታወቃል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version