Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ የሶማሊያ ልዩ ልዑክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ የሶማሊያ ልዩ ልዑክ ጀምስ ስዋን ጋር ተወያይተዋል።
በሶማሊያ የምርጫ ሂደት፣ በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ተልዕኮ የለውጥ ሂደቶችና የአልሸባብን የሽብር ድርጊቶች ማምከን የሚቻልባቸውን ጉዳዮችላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም የሶማሊያን ምርጫ በተመለከተ እንደወዳጅ አገር ሂደቱን በአጽንዖት እየተከታተሉት መሆኑን የገለጹት አቶ ደመቀ÷ ÷ ሂደቱም ሰላማዊ ሆኖ መቀጠሉ እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡
በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ የለውጥ ሂደቶችና የአልሸባብን የሽብር ድርጊቶች ማምከን በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም መክረዋል፡፡
ምርጫውንና በአገሪቱ የተከሰተውን ድርቅ÷ የአልሸባብ የሽብር ቡድን ለዓላማው ማስፈፀሚያ ለማድረግ ቀጣናውን ወደ አለመረጋጋት እንዳይከተው ትብብር ማድረግ አስፈላጊ መሆኑም ተነስቷል፡፡
በሌላ በኩል በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ተልዕኮ የለውጥ ሂደቶችና የሰላም አስከባሪ ኃይል አዋጭ አገራት ሚናን በተመለከተም ምክክር ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version