Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከ33 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከ33 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩን አስታወቀ፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ2014 ዓ.ም የ6 ወር አፈፃፀሙን ለኢፌዴሪ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር አቅርቧል፡፡

በዚሁ ወቅት በቀረበው ሪፖርት እንደተመላከተው÷ ከ104 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚያወጡ ምርቶች ለውጪ ገበያ መቅረባቸውንና ከ80 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጪ ምንዛሬን ማዳን መቻሉን ኮርፖሬሽኑ ገልጿል፡፡

ኮርፖሬሽኑ÷ ከኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት፣ ከውሀ እንዲሁም ከአሰራር ፖሊሲዎችና ከወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታዎች አኳያ ተግዳሮት ያጋጠመው መሆኑ በሪፖርቱ የተመላከተ ሲሆን÷ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችና በቀጣይ ሊከናወኑ የሚገባቸው የትኩረት አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል፡፡

በመድረኩ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴን ጨምሮ የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ ሀላፊዎችና የልማት ድርጅት ስራ አስፈፃሚዎች መገኘታቸውን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version