Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያና ሱዳን በኢነርጂ ትብብር ግንኙነታቸውን ለማጠናከር መግባባት ላይ ደረሱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ከሱዳን የኢነርጂ እና ማዕድን ተጠባባቂ ሚኒስትር መሐመድ አብደላ መሀሙድ ጋር ተገናኝተው በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ሊደረግ በሚገባው ትብብር ዙሪያ መክረዋል።

በዚህ ወቅትም በሁለቱ ሀገራት መካከል በኢነርጂ መስክ ስላለው እምቅ የትብብር አቅም እንዲሁም በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ለሱዳን እያቀረበች ባለው የኤሌክትሪክ ፍጆታ ዙሪያ ተወያይተዋል።

ከዚህ ባለፈም በቀጣይ ኢትዮጵያ ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለሱዳን ስለምታቀርበው ተጨማሪ የኃይልና መሥመር ዝርጋታ ጋር በተያያዘ እየተከናወኑ ስላሉ ተግባራት አንስተው መወያየታቸውን አመላክተዋል።

በዘርፉ የሚደረገውን ትብብር ለማጠናከር እና በጋራ ተቀራርቦ ለመስራት ከመግባባት ላይ መደረሱንም በሱዳን ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version