Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የተለያዩ ኤምባሲዎች በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ዕረፍት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ኤምባሲዎች አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትረያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ዕረፍት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ በቅዱስነታቸው ዕረፍት ሃዘኑን ገልጾ ፥ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የማይተካ ሚና እንዳበረከቱ ገልጿል፡፡

በዚህም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

በሌላ በኩል በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትረያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በማረፋቸው የተሰማውን ሃዘን ገልጿል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version