Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የቀብር ስነ ስርዓት በደብረ ብርሃን ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ በደብረ ብርሃን ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።
 
በቀብር ስነ ስርዓቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እና ብጹዓን አባቶች ተገኝተዋል፡፡
 
ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም በሰሜን ሸዋ ዞን፣ በትግራይና በአርሲ ሀገረ ስብከቶች ቤተክርስቲያንን አገልግለዋል።
 
ብጹዕነታቸው ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በ97 ዓመታቸው ነው ያረፉት።
 
በእታገኝ መኮንን
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version