Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም ያሳለፈው ውሳኔ ትክክለኛ እርምጃ ነው – ቱርክ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑ ለግጭቱ መፍትሔ ለማፈላለግ ትክክለኛ እርምጃ ነው ስትል ቱርክ ገለጸች፡፡

የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንደገለጸው፥ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ የሰብዓዊ ድጋፍን መሰረት በማድረግ ግጭት ለማቆም ያሳለፈውን ውሳኔ አድንቆ ትክክለኛ እርምጃ መሆኑንም ነው ያመለከተው።

ቱርክ ውሳኔው ዘላቂ ሰላም እንደሚያስገኝ ያላትን እምነት ትገልፃለች ያለው መግለጫው፥ የሰብዓዊ እርዳታ ለትግራይ ክልል እንዲሁም ለሌሎች ክልሎች እንደሚዳረስም እምነት እንዳላትም ገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ለሚገኙ የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ የተሳለጠ እንዲሆን ግጭት ማቆሙን ትናንት ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version