Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቢል ጌትስ በምስራቅ አፍሪካ የበረሃ አንበጣን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት 10 ሚሊየን ዶላር ለገሰ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በምስራቅ አፍሪካ የበረሃ አንበጣ መንጋን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት 10 ሚሊየን ዶላር ለገሱ።

ገንዘቡ በዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) አማካኝነት የበረሃ አንበጣን መስፋፋት ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ይውላል ተብሏል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተውን የበረሃ አንበጣ ለመከላከል 138 ሚሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ መግለጹ ይታወሳል።

እስካሁን ድርጅቱ 33 ሚሊየን ዶላር ገንዘብ ያሰባሰበ ሲሆን ለጋሽ ሃገራትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቋል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ በስድስት የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት የተሰከተው የበረሃ አንበጣ በሰብሎች ላይ ከፍ ያለ ውድመት እያስከተለ ይገኛል።

ስርጭቱና እያደረሰ ያለው ጉዳት ከረጅም አመታት በኋላ ከፍተኛው መሆኑም ተገልጿል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version