አዲስ አበባ ፣ የካቲት 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከጣሊያኑ አቻቸው ሉዊጂ ዲማዮ ጋር ተወያዩ።
ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው በሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
ከዚህ ባለፈም ሃገራቱ በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ እንዲሁም በማህበራዊ ዘርፎች ባላቸው ግንኙነት ዙሪያ መወያየታቸውን በጣሊያን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
በዚህ ወቅትም የሃገራቱን ግንኙነት በማሳደግ፥ በልማት ትብብሮች፣ ኢንቨስትመንትና በቱሪዝም መስክ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው አግባቦች ላይ ሃሳብ ተለዋውጠዋል።
በተጨማሪም በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ባሉ ክልላዊ ጉዳዮች እንዲሁም በዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ውይይት አድርገዋል።
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ትናንት ወደ ጣሊያን ማቅናታቸው የሚታወስ ነው።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision