Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሩሲያ እና ቻይና ምዕራባውያን ከዩክሬን ቀውስ ጋር ተያይዞ በሞስኮ ላይ የጣሉትን ማዕቀብ ኮነኑ

FILE PHOTO: Russian Foreign Minister Sergey Lavrov welcomes Chinese Foreign Minister Wang Yi for their talks in Sochi, Russia May 13, 2019. Pavel Golovkin/Pool via REUTERS

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ እና የቻይና አቻቸው ዋንግ ዪ ምዕራባውያን በሞስኮ ላይ የጣሉትን ማዕቀብ አውግዘዋል፡፡
ሰርጌይ ላቭሮቭ÷ ምዕራባውያን ሩሲያ በዩክሬን ላይ በወሰደችው እርምጃ ሳቢያ የጣሉት ማዕቀብ ህገ ወጥ እና ዓላማ ቢስ ነው ሲሉ ኮንነዋል፡፡
ምዕራባውያኑ በሩሲያ ላይ ማዕቀብ መጣላቸውን እና ሀገሪቷን ከዓለም አቀፉ የንግድ ሥርዓት ማግለላቸውን ተከትሎ ሞስኮ ከምንጊዜውም በላይ የቻይናን አጋርነት መሻቷን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
የሁለቱ ሀገራት ሚኒስትሮች በዩክሬን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ በጥልቀት የተወያዩ ሲሆን፥ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኪየቭ ላይ ስለሚካሄደው ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ እና የድርድር ሁኔታ ለቻይና አቻቸው ገለጻ አድርገዋል፡፡
የሀገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሩሲያ እና ቻይና ስትራቴጂያዊ አጋርነታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉና በዓለም አቀፉ መድረክም ድምጻቸውን በአንድነት እንደሚያሰሙ ነው ያስታወቁት፡፡
በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ፣ በሁለትዮሽ ግንኙነት እና ከሌሎች ሀገራት ጋር በሚኖራቸው ጉዳዮች ሁሉ በቅንጅት ለመሥራት እና ወዳጅነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከርም መስማማታቸውን ዘ ናሽናል ዘግቧል፡፡
ሁለቱ ሚኒስትሮች የመከሩት በምስራቅ ቻይና ግዛት አንሁይ ነው፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version