Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮ ባህሬን የንግድና የባህል ፌስቲቫል ሳምንት ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 18፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ ባህሬን የንግድና የባህል ፌስቲቫል ሳምንት ተጀመረ።

በባህሬን የኢፌዴሪ የክብር ቆንስላ ፅህፈት ቤት ኩዌት ከሚገኘው ሚሲዮን ጋር በጋራ የባህል ፌስቲቫሉን አዘጋጅተዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማጠናከርም የፌስቲቫሉ ዓላማ መሆኑም ነው የተነገረው።

በፌስቲቫሉ የኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ብዙነሽ መሠረትና በባህሬን የኢፌዴሪ የክብር ቆንስላ ሀላፊ ወ/ሮ እስከዳር ግርማይ በፌስቲቫሉ መክፈቻ ላይ ተገኝተዋል ።

ለቀናት በሚቆየው ፌስቲቫል ላይም የኢትዮጵያን ባህል የሚያሳዩ አልባሳት፣ የባህል ምግቦችና የሙዚቃ ትእይንቶች ቀርበዋል።

በፌስቲቫሉ አስመጪዎች ፣ ላኪዎች እና የተለያዩ ኩባንያዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

በሰላማዊት ተስፋዬ

Exit mobile version