Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኦነግ የቀድሞ ሊቀመንበር ገላሣ ዲልቦ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የኦነግ መስራች እና አመራር ገላሣ ዲልቦ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ።
ዛሬ ረፋድ የሽኝት መርሀ ግብር ሲ ኤ ምሲ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ጀምሮ የተከናወነ ሲሆን÷ በመርሀ ግብሩ ላይ የቀድሞ የትግል አጋሮቻቸው፣ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል።
ከመኖሪያ ቤታቸው ሽኝት በኋላም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የቀብር ስነ ስርዓታቸው ተፈፅሟል፡፡
ለ45 ዓመታት ያህል በትግል ውስጥ የቆዩትና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት የተከበሩ አቶ ገላሳ ዲልቦ በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።
በቆንጂት ዘውዴ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version