Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ደረጃውን የጠበቀ የአቪየሽን ኢንዱስትሪ ለመገንባት ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ይሰራል – ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ደረጃውን የጠበቀ እና ዘመናዊ የአቪየሽን ኢንዱስትሪ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ለማሳካት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር እንደሚሰራ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ተናገሩ።

ብሄራዊ የአየር ትራንስፖርት አመቻች ኮሚቴ በዛሬው እለት ስብሰባ አካሂዷል።

በዚሁ ወቅት ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ÷ መንግስት በኢትዮጵያ ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ የአቪየሽን ኢንዱስትሪ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ለማሳካት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር መስራቱን እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

በስብሰባው ወቅት በዘርፉ የተደረጉ ልማቶችን በመገምገም በዓለም አቀፉ ሲቪል አቪየሽን ድርጅት መሰረት የዘርፉን ፕሮግራም ከኢትዮጵያ አንጻር ለመከለስ መስማማታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version