Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኢድሊብ በተፈጸመ የአየር ጥቃት 33 የቱርክ ወታደሮች ለህልፈት ተዳረጉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቱርክ በሶሪያ ኢድሊብ ግዛት የበሽር አላሳድ ወታደሮች በፈጸሙት ጥቃት 33 ወታደሮቿ መገደላቸውን አስታወቀች።

ወታደሮቹ በአየር ጥቃት መገደላቸውን አንድ የሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣን ተናግረዋል።

ጥቃቱን ተከትሎም ቱርክ የሶሪያ መንግስት ወታደሮችን ኢላማ ያደረገ አጸፋዊ እርምጃ መውሰድ ጀምራለች።

የሶሪያ ባለሥልጣናት ግን እስካሁን በጉዳዩ ላይ ያሉት ነገር የለም።

ኢድሊብ በቱርክ የሚደገፉት አማጽያን የመጨረሻ ጠንካራ ይዞታ መሆኗ ይነገራል።

አካባቢውን ለመቆጣጠርም የበሽር አላሳድ ወታደሮች በአማጽያኑ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን እየፈጸሙ ይገኛል።

በስፍራው ሩሲያ የአላሳድን መንግስት ስትረዳ አንካራ ደግሞ አማጽያኑን ታስታጥቃለች።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ሩሲያ እና ቱርክ በሶሪያ ጉዳይ ላይ ያላቸው ልዩነት እየሰፋ መምጣቱን መረጃዎች ያመላክታሉ።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Exit mobile version