Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሩሲያ በአሜሪካ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ትጠቀማለች በሚል የቀረበባትን ውንጀላ መሰረተ ቢስ ነው ስትል አጣጣለች

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በአሜሪካ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ትጠቀማለች በሚል የቀረበባትን ውንጀላ መሰረተ ቢስ ነው ስትል አጣጣለች።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ፥ ሩሲያ በዩክሬን እያካሄደች ባለው ወታደራዊ ዘመቻ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ልትጠቀም ትችላለች በማለት መወንጀላቸው ይታወሳል።

በአሜሪካ የሩሲያ ኤምባሲም የቃል አቀባዩ መግለጫ ጠብ አጫሪ ነው፤ ቃል አቀባዩም ያልተረጋገጠ መረጃ ከማውራት ሊታቀቡ ይገባልም ብሏል።

የቀረበውን ውንጀላ መሰረተ ቢስ ነው ያለው ኤምባሲው፥ አሜሪካ ሃሰተኛ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንድትቆጠብም አሳስቧል።

የሩሲያ ጦር በዩክሬን የተሳካ ዘመቻ እያካሄደ ነው ያለው ኤምባሲው ይሁን እንጅ ምንም አይነት የኬሚካል ጦር መሳሪያ ጥቅም ላይ አለመዋሉን አስታውቋል።

መግለጫው ሞስኮ የኬሚካል የጦር መሳሪያዎቿን በፈረንጆቹ 2017 አስወግዳለች ማለቱን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version